ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #101t / Song #101t

የፀሎት ቤት ይሁን

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
የጸሎት ቤት ይሁን ጌታ ይኸ መቅደስህ
የጸሎት ቤት ይሁን ኢየሱስ ይኸ መቅደስህ (2x)
1.
በልጅህ ደም "ሕይወት ሰላም ይሁን!" ብለህ
ለሐጢአታችን ይቅርታን አውጀህ
እግዚአብሔር ሆይ! ታረቅኸን ተመስገን
የክብርህ ማረፊያ መቅደስህ አደረግኸን (2x)
2.
ዙፋንህ በሰማይ የሆነ ንጉሥ
በምድር በእኛ መሃል ስምህ ይቀደስ
የመዓዛ ሽታ መሥዋዕታችንን
ምሥጋናን ተቀበል ከሕይወታችን (2x)
3.
ቅዱስ! ቅዱስ! ቅዱስ! እያሉ መላዕክት በትጋት
ሲያመልኩህ ቀንም ሆነ ሌሊት
ከእኛም ይድረስህ ውዳሴ ማሕሌት
ምልጃም ጸሎታችን ምሥጋና ስግደት (2x)
4.
መቅረዝህም ይንደድ ይታይ ብርሃንህ
የጸሎት ቤትህን ሙላው በክብርህ
አሕዛብም ይምጡ ወደ ጸዳልህ
ይስገዱልህ ድነው በቅዱስ ስምህ (2x)
5.
የዓለም ገበያ እንዳይሆን ማትረፊያ
ቀድሰህ ጠብቀው የአንተን ማደሪያ
የዘለዓለም ሕይወት ፈውስን መቀበያ
ይሁንልን ቤትህ የመንፈስ መኖሪያ (2x)
100%
100%