ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #132t / Song #132t

በክርስቶስ ኢየሱስ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
የእግዚአብሔር ፈቃድ ለልጆቹ
ይህ ነው መንገዱ ለምርጦቹ
ብድራታቸውን ያስተዋሉ
የጌታን መስቀል ይመርጣሉ
በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን
እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ
ስለ ሥሙ ይሰደዳሉ
እንደ ወርቅም ይፈተናሉ
በመጨረሻም ሁሉንም አልፈው
የዘለዓለምን ሕይወት ይወርሳሉ
2.
ለዚች ዓለም የሚመቹ
ነውረኛውን ትርፍ ያከማቹ
በኩርነታቸውን አቃለዋል
በሥጋ ምቾት ተጠምደዋል
3.
ጌታን አክብሮ መጐስቆሉ
እንደ ጉድፍ የትም መጣሉ
የመዳን ምልክት ክብራችን
ድል መምቻችን ነው መስቀላችን
4.
ጌታን ምሰሉ በኑሮአችሁ
ከጠፊ ዓለም ምን አላችሁ
ውጡ ተለዩ እባካችሁ
ፍፁማን ሁኑ በልባችሁ
100%
100%