1.
ከምድር በላይ ቢሆን ከሰማይም በታች
መግባት መውጣታችን ዘወትር ተመልካች
እንደ ኢየሱስ ያለ ማንን አገኛችሁ
የሕይወት ዋስትና ጌታ ሚሆናችሁ
በእምነት እኖራለሁ ጌታዬን አውቃለሁ
የእኔን ፅኑ አምባ ተተግኜዋለው
ወጀቡን ሳልፈራ ታግዬ እረታለሁ
የክብር ሽልማቴን ከእጁ እረከባለሁ
2.
ለነገ አይጨንቀኝም ጭጋግ ቢሸፍነው
ወይኑ ቢጠወልግ ሃሩሩ ቢያሰጋው
ለእግሬ መብራት ነው ቃሉ በእጄ ያለው
የተፈጥሮ አዛዥ ኢየሱስ ሕያው ነው
3.
ፈቃዱ ሲሞላ ጌታዬ ከብሮ ሳይ
ምድር ዕልል ስትል ስያጨበጭብ ሰማይ
መጠለያ ልብሴ እንጀራየ ያ ነው
ነፍሴ ትጠግባለች በክብር በግርማው