1.
ገነት መኖሪያዬን ሰርተህ ውብ አድርገህ
ምግቤን ያለ ድካም እንድበላ ብለህ
ያስቀመጥክኝን ሰው ወሬ ሲደልለኝ
እጦት ሲያራቁተኝ በቸልታ አትየኝ
ባስቀመጥከኝ ቦታ ፀንቼ እንድቆይ
መጥተህ ስትጐበኘኝ በእኔ ደስ እንዲልህ
ፀጋህን አብዛልኝ ጌታ ሆይ እባክህ
2.
ልቤ እየቸኮለ እግሬ ሮጥ እያለ
ውርደትን ለማየት ዓይኔ እየከጀለ
ድንበር እየጣሰ ከኃጢአት እየዋለ
የማታ የማታም ሚዛኔ ቀለለ
3.
የጭንጫ ቡቃያ ፈጥኖ የበቀለ
ፀሐይ ስትወጣ ነዶ ተቃጠለ
አንተን ሆኜ እኔ ፍሬን እንዳፈራ
አንስተህ አትጣለኝ የእኔ ጌታ አደራ
4.
ቸኮል ያለ ሳዖል በዓይኖችህ ተንቆ
ብላቴናው ዳዊት ተቀብቷል ልቆ
ዓይኔን ግለጥና ስፍራዬ ልወቀው
አሳድገኝ እንጂ ዕድሜዬን አትቁረጠው