ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #125h / Song #125h

መድኃኒቴ ልከተልህ

I Will Follow Thee My Saviour

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
መድኃኒቴ ልከተልህ
በታዘዝሁበት ሁሉ
በምትሄደው ልከተልህ
ልከተልህ በሁሉ
ልከተልህ መድኃኒቴ
ደምህን አፈሰስህ ለኔ
ሰው ሁሉ እንኳን ቢክድህ
በፀጋህ ልከተልህ
2.
መንገዱ ቢታጠር በሾህ
ቢጠፋብኝም ዱካህ
መንገዱን ጠርገህልኛል
በደስታ እንድከተልህ
3.
መከራ እንኳ ቢያግደኝ
ክፉኛም ቢፈትነኝ
የተፈተንኸው ትዝ አለኝ
ልከተልህም ደስ አለኝ
4.
ወዳዘንም ብትመራኝ
ድኃ ምስኪንም ብሆን
አንተም እንዲህ ሁነህ ነበር
ስለዚህ ልከተልህ
5.
በጥልቅ ዮርዳኖስ ብትወስደኝ
በውርጭ ስፍራም ብትመራኝ
አንተ በፊቴ ስላለፍህ
ፀንቼ ልከተልህ
100%
100%