ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #193t / Song #193t

እግዚአብሔር ኃያል

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
እግዚአብሔር ኃያል
በሰልፉም ደግሞ ኃያል
ከቶ እስከ ዛሬ ለማን ተረቶ ያውቃል (2x)
1.
ህዝቡን ከልሎ የሚዋጋ
ለጠላት ዛቻ የማይሰጋ
ብድራትን መላሽ የእኛ አምላክ
ይርታ እንጂ መረታትን አያውቅ (2x)
2.
የእምነት ባለድል ሳይጸጸት
ጌታን አምኖ ሰው አያፍርበት
ለተስፋው ፈቶ ሰንሰለት
ሕይወቱን ሰጥቷል ሳትሰስት (2x)
3.
አንተም በኃይሉ ድል ነስተህ
በእቶን ተፈትነህ ነጥረህ
ለመንግሥቱ ብቁ ሆነህ
እንድትወጣ ጌታ ይርዳህ (2x)
4.
ያን ጊዜ ተዋግቶ የረታ
የጠላቱን ጅማት የፈታ
በፅኑ አመታት የሚመታ
ሁሉን የሚችል የድል ጌታ (2x)
100%
100%