ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #162t / Song #162t

ኢየሱስ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ኢየሱስ ኢየሱስ የነፍሴ መድኃኒት የሰላሙ ንጉሥ
ኢየሱስ ኢየሱስ ና ሕይወቴን ፈውስ
1.
ወደ እኔ ጩህ እኔም እመልሳለሁ
ታላቁንም ነገር ለአንተ አሳይሃለሁ
በቃልህ ስላልከኝ እንዲህ እጮሃለሁ
እንድትፈውሰኝ ሥምህን ጠራለሁ
2.
በድካም ማዕበል ሕይወቴ ተገፍቶ
በሚሰብር በትር ክፉኛ ተመቶ
የታመቀው ስቃይ ልብን እየጣሰ
እንባን አስክትሎ ወደ አንተ ደረሰ
3.
አልጥልህም ብለህ ከቶም አለቅህም
የገባህልኝ ቃል አልተዘነጋኝም
እኔ ፈዋሽህ ነኝ ብለህ የፈወስከኝ
ከጉስቁልናዬ ና ዛሬም አድነኝ
4.
ሰባራውን ጠጋኝ የፈረሰውን አዳሽ
ፈዋሼ አንተ ነህ የእንባዬ አባሽ
ሰዎች ያላዩትን ቁስሌን ያየህልኝ
አንተ ብቻ እኮ ነህ ዛሬም ያለህልኝ
100%
100%