1.
ወንድሜ ታማኝ ሁን
የሱስ ይመጣል
እስከ ዛሬ የጠበቅነው
በቅርብ ወደ ቤታችን እንገባለን
የድል መዝሙር ልንዘምር
2.
ወንድሜ ታማኝ ሁን
አትጠራጠር
ያሳየን ፍቅር ታላቅ ነው
ለዚህ ፍቅሩ
ፍጹም ወደር የለውም
እኛን ሊያድነን ሞተ
3.
ወንድሜ ታማኝ
ዋጋ እንድታገኝ
ላንተ የተዘጋጀውን
ታማኞች ያንን ክብር ሊቀበሉ
ዕረፍትም ሊሰጣቸው ነው
4.
ወንድሜ ታማኝ ሁን
ብዙ አትቆይም
በስቃይና በድካም
የድካምህ ጊዜ እያለፈ ነው
ለዚያ ቀን አሁን ተዘጋጅ
5.
ወንድሜ ታማኝ ሁን
በቅርብ ይመጣል
የምድራችን ታላቅ ንጉሥ
ትዕግሥትም ይኑርህ
እርሱ እስኪ መጣ
ዋጋህንም ታገኛለህ
6.
ወንድሜ ታማኝ ሁን
ጊዜው ተቃርቧል
ዋጋህን የምታይበት
ከጌታ ጋር ሁን
ምን ጊዜም ቢሆን
ዋጋህን እንድትቀበል