ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #137t / Song #137t

የባዘንከው ውድ ወንድሜ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
በከንቱ ሮጠህ ጉልበትህ ባክኖ ጨርሶ አልቆ
በኃጢያት ሸክም ነፍሽ መንምና አጥንትህ ደርቆ
መድረሻህ ጠፍቶብህ ግራ ገብቶህ የምትባዝን
የዓለምን ቤዛ ቀርበህ አማክረው ጌታ ኢየሱስን
የባዘንከው ውድ ወንድሜ
አዳምጠኝ እስኪ ልምከርህ ደግሜ
ወደ ነፍስህ እረኛና ጠባቂ ና ተመለስ
2.
ያለማወቅን ወራት ዘመናት እና ዓመታትም
ከኢየሱስ ወዲያ እርካታ ላይገኝ እንዲያው ስታልም
በዓለም የሚያንፅ ከቶ አይገኝም ምን ይሻልሃል
ድንቁ ኢየሱስን ተቀበለው ያረካሃል
3.
ዕውቀትን አጥተህ በዚች ዓለም ላይ የተንከራተትክ
በጨለማው ገዥ በዲያቢሎስ እጅ የተማረክ
ምርኮን ለመካፈል ከላይ ከሰማይ የወረደው
የምስራቹን ትፈልታለህ አማኑኤል ነው
100%
100%