1.
ቤቱ ፈርሶ እያየህ የእግዚአብሔር
የራስህን ኑሮ ልታሳምር
ያለጌታ ልትከብር ሮጠሃል እስከዛሬ
ውስጡ ግን ባዶ ነው የጨበጥከው ፍሬ
የጠፋውን ማን ይፈልጋል?
የተጐዳውን ማን ያክማል?
ሰባራውን ማን ይጠግናል?
የፈረሰውን ማን ያድሳል?
2.
በጐቹ ለአራዊት መብል ሆኑ
እረኛ በማጣት ተበተኑ
ራስህን ስታሰማራ ፤ ለምቾትህ ስትሠራ
ይታይህ ወዳጄ የመንጋው መከራ
3.
መክሊትህ ወዴት ነው? ወንድሜ ሆይ!
እንደ ሃኬተኛ ቀበርከው ወይ?
የሰጠህ ይጠይቅሃል! አደራውን የት አድርገሃል?
የምትጠፋውን ነፍስ ከእጅህ ይፈልጋል
4.
ነፍስን ሊሰበስብ የተጠራ
ለጠፉት የሚያዝን የሚራራ
የምሥራች የሚያወራ
በፍጻሜው ይሸለማል
ዘለዓለም ይደምቃል እንደ ሰማይ ጸዳል