ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #141t / Song #141t

ድል ለማድረግ ወጣ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
1.
የፈርዖን ገንዘብ ያልማረከው ጀግና
ዓይኑ ያልደከመ ያላለቀ ገና
ድል ለማድረግ ወጣ በጦርነት ሲቃ
በጀርባው አንግቦ የአምላኩን ጦር ዕቃ (2x)
2.
የወይኒው አስራት የግርፋት ብዛት
አልቻለው ሊያበርደው የፍቅሩን ትኩሳት
ፎከረ ያ ጐበዝ ሊጥል ሊገረስስ
ጠምዶ በቀኝ እጁ የቃሉን መትረየስ (2x)
3.
የልብ ዓይኑ ፈጦ ትኩር ብሎ እያየ
የጠላትን ምሽግ ሰፈሩን አጋዬ
የአርያም እሳት በኃይል ጐብኝቶታል
እባቡና ጊንጡን ከእግሩ ስር ረግጦታል (2x)
4.
በድካም በረታ ጅማቱ ጠንክሯል
አንገብግቦት ፍቅሩ ወኔው ተቀስቅሷል
በጀርባው መተልተል ጌታን አከበረ
የሞትንም ባሕር በእምነት ተሻገረ (2x)
100%
100%