ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #84t / Song #84t

ሁሉን የምትገዛ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
1.
የጽድቅ ሥራህን ጌታ ሰራህና
በጨለማ ላሉ ፀሐይ ወጣችና
ከዘለዓለም ጥፋት አንተ ያዳንካቸው
በታዳጊነትህ እጅግ ደስ አላቸው (2x)
ሁሉን የምትገዛ ያለህ የነበርህ
ትልቁን ኃይልህን ለብሰህ የከበርህ
ሥምህ ለዘለዓለም ይመስገን ይባረክ
ጉልበት ሁሉ ለአንተ ጌታ ሆይ ይንበርከክ
2.
የመስቀል ፍቅርህን ለሰው ይነግራሉ
የቅድስናህን ክብር ያወራሉ
በክንፎችህ ጥላ ታምነው ይኖራሉ
የማዳን ክንድህን ሁልጊዜ ያያሉ (2x)
3.
ከሥም ሁሉ በላይ ሥምህ የከበረ
ከሰው ልጆች ይልቅ ውበትህ ያማረ
የሚመስልህ የለም እጅግ ልዩ ነህ
ከፍ ብለህ ንገሥ ግርማ ተሞልተህ (2x)
4.
ክብርህ በምድር ሁሉ ይታይ አምላካችን
ምላስም ይመስክር ታላቅነትህን
በሰማይ በምድር ትሰለጥናለህ
ሁሉም ከእግርህ በታች አንተ ትገዛለህ (2x)
100%
100%