1.
የሚቀጠቅጥ በአንተ ላይ ወጥቷል በጠላት ተከበሃል
ክርስቲያን ተጠንቀቅ ዙሪያህን አስተውል
ጉልበትህ አይላላ ጠንክረህ ተዋጋ
ብድራትን አይተህ ያለልህን ዋጋ
ኢየሱስን ለብሰህ
የጦር ዕቃህን አንስተህ
በእርሱ መልካም ጦርነት ተዋጋ
ኢየሱስ ያሸንፋል ለድሉ አትስጋ
2.
በጦርነት ላይ መቁሰልም አለ ሞትም ቢሆን ጥቅም ነው
ለጨለማው ገዢ እጅህን አትስጠው
እስከ ሞትም ታመን ነፍስህን አታክብራት
ለታመነው ፈጣሪ አሳልፈህ ስጣት
3.
ባለጋራህ ዲያብሎስ ሊውጥህ እያገሳብህ ነውና
ከድምፁ አትፍራ አባትህ አለና
መንጋጋውን ዘግቶ ከአፉ ያስጥልሃል
ከቶም እንደማይጥልህ በግልጽ ያሳየዋል
4.
የውጊያው ጊዜ አሁን ነው ወንድም
ተነስ ተጋጠመው ድል ትነሳዋለህ
በርትተህ ታገለው የአብርሃም አምላክ ጋሻ ይሆንሃል
ለአገርህም አብቅቶ አክሊል ይሰጥሃል