ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #145t / Song #145t

ምህረቱ አያልቅምና

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 4
1.
በባቢሎን ወንዞች ማዶ አዝነን ተቀምጠን
ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ እጅግ አለቀስን
የመጽናናት አምላክ ከላይ ግን ያየናል
እንባችንን ጠርጐ ስብራታችንን ይጠግንልናል
ምህረቱ አያልቅምና
ለዘለዓለም ቸር ነውና
የማዳን ኃይሉን ላሳየን
በክንዱ ለሚጐበኘን
መልካሙን መዓዛ በምሥጋና አቅርቡለት
በዕልልታ ስገዱለት
2.
የችግረኞችን ጩኸት ሰምቶ አይጨክንም
ምርጦቹን ከልቡ በፍፁም አያስጨንቅም
ጠላታቸው ሊበትን በነጐድጓድ አንቀጥቅጦ
ረድኤታቸው ከተፍ ይላል ከሰማያት በግርማው ተገልጦ
3.
በሥጋዎቻቸው የገነኑ ፈፅመው ሲወድቁ
እግዚአብሔርን በመታመን የሚጠባበቁ
በእንባቸው ፍሬ እያሸበረቁ
በክንፍ ይወጣሉ ይሮጣሉ ይከብራሉ እንደ ዕንቁ
4.
ለእኛ መጠጊያችን ጌታ እግዚአብሔራችን
በምንም አንፈራም እርሱ ኃይላችን ነው
ከሰይጣን አሽክላ ሥሙ ይጠብቀናል
ለአሞራም ሳይሰጠን በክንፎቹ አዝሎ ቤቱ ያገባናል
100%
100%