1.
እሥራት ሰይፍና እሳትም ቢኖር
ያባቶች ሃይማኖት አለን
ልባችን በጣም ይደሰታል
ይህን ግሩም ቃል ሲሰማ
2.
ያባቶች እምነት
ፅኑ እምነት
እስከ ሞት
ባንተ መታመን
3.
በጨለማ አባቶች ቢታሰሩም
ልባቸውን አንተ አበራህ
የልጆቻቸው ፍጻሜ ያምራል
አንተን አጥብቀው ቢይዙ
4.
ያባቶች እምነት
ፅኑ እምነት
እስከ ሞት
ባንተ መታመን
5.
የጥንቱ ሃይማኖት ፍቅር አለው
ትእግስትም የተሞላበት
የማይናወጥ የማይጠፋ
በየቀኑ የሚሠራ
6.
ያባቶች እምነት
ፅኑ እምነት
እስከ ሞት
ባንተ መታመን