ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #179t / Song #179t

እግዚአብሔር መንፈስ ነው

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
እግዚአብሔር መንፈስ ነው በሥጋም አይደፈር
እጅግም ታላቅ ነው በሰው የማይገመት
ዛሬም እንደቀድሞው ክንዱ ኃያል ያደርጋል
ቢወዱም ቢጠሉም ኢየሱስ ይነግሣል
በሰማይ በምድርም ሙሉ ስልጣን ያለው
የሚለውጥህ እንጂ የማይለውጠው
አልፋ ኦሜጋ ማለት ጌታ ኢየሱስ ነው
2.
ሥሙን በመታመን ሲቀርቡት ይቀርባል
በደከመች ሕይወት ብርታት ይጨምራል
ሞገዱን ፀጥ አድርጐ ሰላምን ይሰጣል
ምንጩን አጠጥቶ በረሃን ያለማል
3.
የማይታየው ባህሪ የዘላለም ኃይሉ
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በእውነት ሲያስተውሉ
ከጥንትም ጀምሮ ከተሰሩት ደምቆ
ይኖራል ኢየሱስ ህልውናው ታውቆ
4.
የተዓምራት አምላክ ክንዱ መች አጠረ
ሰው ያወቀ መስሎት ብዙ የመረመረ
ኃጢአትን አጣጥሞ ለፍርድ እየኖረ
ጌታን የለም ብሎ እጁን አጣመረ
100%
100%