አንተን አንተን ብዬ
እኔን ወደ ኋላ ጥዬ
በእምነት እሻገራለሁ
በድል ፊትህን አያለሁ
1.
ከቀደሙት ተምሬያለሁ
የአንተን ተስፋ እጠብቃለሁ
በምሕረትህ ተመልከተኝ
እምነትንም ጨምርልኝ
2.
የፍየልን ሌጦ ለብሰው
መስቀልህን ተንተርሰው
እየተንከራተቱ ብዙ አሉ
ክብራቸውን ለአንተ የጣሉ
3.
በእምነት ሥምህን ጠሩ
በፀሎት ለአንተ ነገሩ
ከላይ ሆነህ ሰማሃቸው
ቃላቸውን አደመጥካቸው
4.
በእምነት ባሕርን ከፈሉ
ከጠላት እጅ አመለጡ
እነርሱን ልመስል እሻለሁ
በእምነት ሥምህን ጠራለሁ
5.
በመንፈስ መልዕክትን ሰሙ
ጌታ አንተን ተሳለሙ
እምነትን ስጠኝ እላለሁ
እኔም አንተን ለምናለሁ