ዘመኑ ፈጠነ ሮጠ ገሰገሰ
የጌታችን መምጫ ጊዜያቱ ደረሰ
ሰዎች ቶሎ በሉ መከሩን ሰብስቡ
የተጣለብንን አደራ አስቡ
1.
ሰዓቱ ሊሞላ በቅርብ ነው ያለው
መለከት ሊነፋ በቅርብ ነው ያለው
ነገሩ ሊያከትም በቅርብ ነው ያለው
ጌታም ከተፍ ሊል በቅርብ ነው ያለው
2.
ሰማያት ሲከብዱ ደመናው ሲጠቁር
ምድራችን ስታምር ነገር ሲቀያየር
ምን አዚም ኖረብን እንዳናይ ጊዜ አጥሮን
ተው ነቃ እንበል እናቁም አንቅልፍን
3.
ሰዉ ሲተራመስ ሞትን ለመሳለም
ከአምላክ ተለይቶ በኃጢያት ሲታመን
ጠቢቡ እንኳን ሲስት በሰይጣን ሲታለል
ተነሱ አንናገር ለነፍስ እንታገል
4.
ለራሱ ያልሞተ እራሱን ያልከዳ
ጌታ የማይገዛው ለኃጥያት ያልታገለ
በምኑ ይመስክር ልቡ ይንቀጠቀጣል
ዋጋም ክፈል ሲባል ትቶ ይፈረጥጣል