ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #106t / Song #106t

ከዚህም የሚበልጥ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ከዚህም የሚበልጥ
የጌታ ኃይል ሲገለጥ
እናያለን ገና የክብሩን ደመና
ምድር ስትሞላ በጌታ ምሥጋና
1.
ጌታ በመንፈሱ በቅሉ መርምሮ
ሥራችንን ሁሉ ቢነግረን ዘርዝሮ
በዕውቀቱ ተደንቀን በኑሮአችን አፍረን
ንስሐ ገብተናል "ይቅር በለን" ብለን
2.
ኃጢአታችንን በደሙ አነጻው
የእኛ ጌታ ኢየሱስ ይቅርታው ብዙ ነው
ርኩስ መናፍስትን በኃይሉ ያስወጣል
በወንጌሉ ሥልጣን መንግሥቱን ያሰፋል
3.
"ጌታ ሆይ!" እያለ ለሚቃትተው
ማዳኑ ሊመጣ ጽድቁ ሊገለጥ ነው
የእግዚአብሔር ምሕረት ሁሉንም አብስሩ
የበረከት ዝናብ ይኸው ውሽንፍሩ
4.
ረሃብተኛ ሲመገብ ልኡል ቃሉን ሲሰጥ
በጻድቅን ዕልልታ ምድር ስትናወጥ
በምሥጋና ዜማ በደስታ ዝማሬ
በታላቁ መከር የአገልግሎት ፍሬ
100%
100%