ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #171t / Song #171t

እንዲህ አልነበርኩም

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
እንዲህ አልነበርኩም ዛሬ ግን ሆኛለሁ
ያን መልካሙን ሕይወት ከድሮ ውስጥ ፈልግያለሁ (2x)
1.
ሥምህን እንደዋዛ ተሽክሜዋለሁ
ክርስቲያን ተብዬም ይኸው እጠራለሁ
ውስጤ ቢመረመር ግን እንዲህ አይደለም
የመንፈስ ፍሬ ከቶ በእኔ የለም
2.
የለየልኝም ከሃዲ አልሆንኩኝም
ክርስቲያንም ሆኜ አልበረታሁም
እንዲያው ለብ ብዬ አስቸግሬያለሁኝ
ዛሬስ በንስሃ ተደፍቻለሁኝ
3.
ለክርስቲያኖች ለአንተ ያለኝ ፍቅር
ላገልግልህም ሥምህን ላስከብር
የነበረኝ ፀሎት ያ ሁሉ ትጋቴ
እፍገመገማለሁ ከድቶኛል ብርታቴ
4.
ሽቅብ እንደመውጣት ቁልቁለት ሄጃለሁ
ወደ ሞትም ደጃፍ በጣም ቀርቤያለሁ
አሁንም በቃልህ ተገስጫለሁኝ
ዳግም አንሳኝ ብዬ ተማጽኛለሁኝ
100%
100%