ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #110t / Song #110t

የአምላኩ ፈቃድ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
የአምላኩ ፈቃድ ፈቃዱ ሆኖ
በፍጹም ነፍሱ በጌታ ታምኖ
በነገር ሁሉ ሕይወቱ ረክቶ
ጻድቅ ይኖራል በቃሉ ጸንቶ (2x)
1.
የሥጋ ምኞት የዓይንም አምሮት
የዓለም ፍቅር ልቡን አታልሎት
በጌታ መሆን ሞኝነት መስሎት
ክርስትናዉን አውልቆ ጥሎት
ያንን ሰው እዩት ሲሮጥ ወደሞት
2.
የጌታን ፈቃድ ቀድሞ እየሮጠ
በምኞት ባሕር ገብቶ ተዋጠ
ዝናን ፍለጋ ሄደ ዋተተ
እርካታን ጥሎ እየከነፈ
እንደተጠማ ሳይረካ ሞተ
3.
እንግዳው ሰው ሆይ ! የምድረበዳው
የማይረባህን የምትመኘው
ማንነትህን የዘነጋኸው
ምኞት ኃጢአትን ኃጢአት ሞትን
እንደምትወልድ እንዴት አጣኸው?
4.
የሥጋ ሩጫ ከእንግዲህ በቅቶ
ከንቱ መባከን ከእንግዲህ ቀርቶ
አርፈህ ተገዛ ፈቃዱን አውቀህ
የጌታን ምክር ቃሎቹን ንቀህ
እንዳትቀጣ ዳግም አምጸህ
100%
100%