1.
ጌቴ ኢየሱስ የእኔ ቤዛ
ጉስቁልናዬ ቢበዛ
ከክብሩ ተዋረደልኝ
በእኔ ፈንታ ታረደልኝ (2x)
የእኔ ጌታ ስለ እኔ ገዶት
ኃጢአቴም አስጨንቆት
ዝም ብሎ እንደ ጠቦት
በሀሰት ተመስክሮበት በችሎት
ዕዳዬን ከፍሎታል ተሰቅሎ በመሞት
2.
ግብዝ አይደል እንደ ሰው
ወረት ጨርሶ ያልነካው
በጐልጐታ ላይ የታየው
እውነትም እርሱ ፍቅር ነው (2x)
3.
ያጀቡት ሁሉ ፈርጥጠው
ለሰይፍ ለጐመድ አጋልጠው
በዚያን ምሽት አልቦታል
ቃቶ ነፍሴን ታድጓታል (2x)
4.
በግፍ ጀርባው ተላልጦ
እግሩንም ለስቃይ ገልጦ
ንጹስህ ደሙን ለእኔ ከፍሎ
በቀራንዮ ደርቆ ውሎ (2x)
5.
ይህ ፍቅር በሕይወቴ ገብቶ
የደህንነት ሥራ ሰርቶ
ቆሻሻነቴን ቀይሮ
አይቻለሁኝ ውብ ኑሮ (2x)