ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #112t / Song #112t

በደልን ይቅር የሚል

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
በደልን ይቅር የሚል አመጻን የሚያሳልፍ
ከጥፋት ሊያድናቸው በሕዝቡ ላይ የሚሰፍፍ
እንዳንተ ያለ አምላክ ማነው ምህረቱ የበዛ?
ቅዱሳንህ ሲሰደዱ መከራውም ሲበዛ
ርስትህን ለማላገጫ አሳልፈህ አትስጥ
የተቀደሰ መቅደስህን በጠላት አታስረግጥ
2.
የእግዚአብሔር ዕድል ፈንታ ተፅፏል ህዝቡ ነው !
ሊያመልከው ሊያገለግለው ከግብጽ አገር ያፈለሰው
አርነቱን በባርነት ሊተካ የሚከጅለው
"ይገባኛል " የሚል ማነው ? ሕዝቡ የእግዚአብሔር ነው!
3.
እስከዛሬ ከብረሃል በአህዛብ ተፈርተሃል
የጠላትን እርግማን በረከት አድርገሃል
የአሳዳጁን ፈረሶች በባሕር አስጥመሃል
በክንድህ ተከላክለህ ርስትህን ጠብቀሃል
100%
100%