ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #187t / Song #187t

የባዘነውን ፈላጊ አምላክ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
1.
የጠራውን መስሎ መኖር መጋደሉን ፈርቶ
የገባለትን ቃልና ተስፋውን ዘንግቶ
የሙት ልጅ የነበረ ሰው ከጥፋት የዳነ
የተሰዋለትን ኢየሱስ ያንን አዳኙን ከዳ
የባዘነውን ፋላጊ አምላክ
የምህረት አምባ ለጠፉትም የምታነባ
ከሕይወት ወደ ሞት ከእረፍት ወደ ጭንቀት
የሄደውን መልስ እባክህ ጌታ ወደ መንጋህ በረት
2.
ተዋግቶ የማረከውን ያንን ስመ ጥሩ ጀግና
ጌታውን ሊያስከብር ቆርጦ ተሰልፏልና
ጠላት ከባሻገር ቆሞ ቅናት እያጋየው
እሸክላውን ዘርግቶበት ወንድሜን ዘለፈው
3.
በአምላኩ መቅደስ ውስጥ ሆኖ ተማምኖ እያገሳ
ገናናነቱንም ሲያውጅ የይሁዳን አንበሳ
እንግዳ ነገር ወሰደው ነዝንዞ ጨቅጭቆ
ፀጋ ክብሩን አስላጭቶ እጅግ አስጨንቆ
4.
ጥቃቅኑ ነገር ሁሉ ጉልበቱን ከርክሮ
ጤናውን እየሰቀረበት በህመም አደንዝዞ
ያ የክህደት አውሎ በሕይወቱ ነፍሶበት
ከወይኑ ግንድ ገነጠለው ፍሬ እንዳይገኝበት
100%
100%