ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #139t / Song #139t

መጥቷል በንስሃ

english translation

ምድብ / Category: ታማኝነት / Loyalty
ደራሲ / Author: ተስፋዬ ጋቢሶ
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
1.
ሊጠፋ የነበር በኃጢያቱ ረክሶ
ለጥቂት አምልጦ ከዓለም ተመልሶ
ማንነቱን አውቆ ልብ ገዝቶ ኖሮ
ባለፈው ጥፋቱ በጸጸት ተማሮ
መጥቷል በንስሃም የጌታን ቃል ሰምቶ
ሰይጣንን ዓለምን ሥጋን ተሰናብቶ (2x)
2.
እንዲያው ሲግደረደር ጥማቱን ደብቆ
የጭንቀቱን ግፊት በሆዱ አምቆ
ሰላምን ለማግኘት ሲባዝን ሰንብቶ
ከሰላም አለቃም መንገድ ተገናኝቶ
አሁን ወጥቶለታል ችግሩን ተንፍሶ
ተጽናንቶም ይኖራል ሕይወቱ ታድሶ (2x)
3.
ወዶታል ከአንጀቱም ተመክቶበታል
ጌታም በጠላት ፊት በዘይት ቀብቶታል
ከትቢያ አንስቶ ሞገስን ሰጥቶታል
በድል አየመራው ከዚህ አድርሶታል
እንደ ሰባ እንቦሳም በደስታ ይዘላል
እየፈነደቀም ሀሌሉያ ይላል (2x)
4.
ጠቢባን ግንበኞች ወደ ጐን የጣሉት
አይጠቅመንም ብለው በንቀት የካዱት
የናዝሬቱ ኢየሱስ ግን የማዕዘን አለት
ሆኖለታል ለእርሱ የሕይወት መሰረት
ከዳንኩኝስ ብሏል አዲስ ሰው ከሆንኩኝ
ዘመድ ወዳጆቼ ያሉትን ይበሉኝ (2x)
100%
100%