የሱስ ካለ ሠላም አለ
የሱስ ካለ እርካታ አለ
ደስታና ዕረፍትም እሱ ጋ አለ
1.
ባህር ላይ መርከቧ ስትናጥ
የመኖር እድሏ ሲሟጠጥ
ማዕበሉን አዞ ፀጥ ያረገው
የሱስ ነው ልጆቹን ያዳነው
2.
አጋርም በተሠጣት ምድር
ተጨንቃ አጥታ ምንም ነገር
ስታለቅስ ከሠማያት ሰምቶ
አዳናት የሱስ ጣልቃ ገብቶ
3.
ጉልበት ሁሉ ለርሱ ይሰግዳል
ንፋስም ይታዘዙለታል
ለየሱስ የሚያቅተው የለም
ተከብሮ ይኖራል ዘላላም
4.
ምንድነው ከቶ የሚያስፈራኝ
ራብ ወይስ እጦት ችግር ስቃይ
የሱስን ካገኘሁ ይበቃኛል
ሁሉም ነገር እርሱ ጋ ይገኛል