እኔስ ተስፋና ያለኝ ምኞቴ
ተጋዳይ መሆን ነው እስክደርስ ቤቴ
1.
የሚቤዝኝን የሕይወትን ዕንቁ
ቢያጥላሉብኝም ሰዎቹ፣'ሳያውቁ
እኔስ አይቼው የሕይወትን ተስፋ
መሮጥ ይዣለሁ ኋላ እንዳልጠፋ።
2.
አምላክ የለም ቢሉ እኔን ላይገደኝ
የጠላት ጥበብ ላይቆጠቁጠኝ
ይህን ሥጋዬን እጐስማለሁ
ዛሬ ባለቅስም ነገ እሥቃለሁ።
3.
የእምነትን ተስፋ ፍቅሩን ጨብጬ
ሜዳ ዳገቱን ባለም እሮጬ
ታማኝ ባሪያ ነው መባል ናፍቆኛል
የደም ዋጋ ነኝ መች ይጠፋኛል።
4.
የዓለም ወርቅ ዕንቁ ምኞት ላይሞላ
መሸሽ ሲጀምር ሊያልፍ እንደ ጥላ
እኔስ ተስፋና ያለኝ ትምክሕቴ
ከሁሉም በላይ ጌታን ማግኘቴ።