ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #168 / Song #168

አንድ ጊዜ ከጌታ አንድ ጊዜ ከአለም

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
አንድ ጊዜ ከጌታ አንድ ጊዜ ከአለም
የክርስቲያን ኑሮ እንደዚህ አይደለም
ይህማ ከሆነ ወንድም ክርስትና
ዋጋ የለሽ ይሆናል አይገኝ ዋስትና
1.
የስም ክርስትና ብይዝ ተሸክሜ
ህይወትን ላያስገኝ ከንቱ ነው ወንድሜ
ያለም ብርሃን ሳልሆን ጨለማ ሆኛለሁ
ዋይ ለእኔ ጌታዬን አሳዝኛለሁ
2.
ስናገር ስዘምር ስሜ ክርስቲያን ነው
ከቤቱ ስወጣ ሥራዬ ሌላ ነው
ዓለም ከዚህ ሌላ ታዲያ ምን ያደርጋል
የእኔስ ክርስትና በምን ይታወቃል
3.
ቢሆን አንድ ባሪያ ለሁለት ጌታ
እንዴትስ ይሆናል ለአንዱ ካልተገዛ
ብርሃን ከጨለማ ምንስ ህብረት አለው
ክርስቲያን በሥራው ጌታን ካልመሰለው
4.
ጌታን እንዳልተወው ህይወትን እሻለሁ
አለምን እንዳለተው ገንዘብን እወዳለሁ
በሰው ዘንድ ሲታይ ትኩስና በራድ
ደቀመዝሙር ነኝ ገንዘብን የምወድ
5.
የአምልኮ መልክ ይዤ ኃይሉን ግን ክጃለሁ
ለተመለከተኝ ክርስቲያን እመስላለሁ
ጌታ የሱስ ልብን የሚመረምረው
የእኔን ክርስትና እርሱ ነው የሚያውቀው
100%
100%