ፃዲቁም ይድደቅ እርኩሱም ይርከስ
የሚባልበት ሰዓቱ ሳይደርስ
ቀን ሳለ ዛሬ በቃሉ እንደግ
በንስሃ ህይወት ወደእርሱ እንለፍ
1.
ሊቀካህናችን ከመቅደስ ሳይወጣ
የምህረት ደጅም ፈጥኖ ሳይዘጋ
ራሳችንን አስጨንቀን በንስሃ እየተዋረድን
ልንጠብቀው ይገባናል
2.
ጌታ ጌታ ሆይ ብቻ እያልን
ፍቃዱን ማድረግ ጭራሽ ተስኖን
በለብታ ህይወት ተዘፍቀን ሳለን
ቀኑ ደርሶብን ጌታ እንዳይተፋን
3.
ቸልተኝነት እኛን አጥፍቶን
ለኃጢኣታችን ንስሃ ረስተን
የጽድቅን ኑሮ ሳንለማመድ
እንደይቋረጥ የእርሱ ማማለድ
4.
እንተራቆትን ዛሬ ተረድተን
አልብሰን ብለን ጌታን ተማጽነን
በጽድቅም መንገድ በእምነት ተጉዘን
ከሚድኑቱ ጐን እንድንገኝ
5.
ኩራዛችንን በዘይት ሞልተን
መብራታችንን ዘውትር አብርተን
ከልባሞቹ ጋር ተደምረን
በሠርጉ እንገኝ ሳይዘጋብን