ዛሬ ተነስ ሳያልፍህ ዘመኑ
ቀጠሮ አትስጥ አሁን ነው ሰዓቱ
የመዳን ቀን ዛሬ ነው ጊዜያቱ
1.
አምላክህን አስቀድም በሰጠህ አእምሮ
ወንድም አትጨነቅ ለምድራዊ ኑሮ
ጣኦትን አታምልክ የዘመኑን ብልጭልጭ
ነፍስህን ጠብቃት እንዳትሆን ቀላጭ
2.
የዲያብሎስ ባንዲራ የወገን መዋጊያ
የገንዘብ ሀብት ሆኗል የሰው ልጆች መጥፊያ
ምርጫህ ዛሬ ነው ሳለህ በሕይወትህ
ድንገት እንዳይዝህ የሥጋዊ ሞት
3.
ሕይወትን አስረክብ ለባለአደራ
የፍቅር አምላክ ነው ለሁሉ ሚራራ
ሁሉን ነገር አርሣው ያለምን መከራ
ወገብህን ታጠቅ ለወንጌል አዝመራ