የማዕድህ አሳላፊ የጊዜው ተረኛ ካህን
ከአንተ ከታላቅ አምላክ ታላቅ አደራ የተቀበልኩ
ነገር ግን መትጋት አቅቶኝ ለመውደቅ እየተቃረብኩ
1.
ሁሉም ለየብቻው ሲጠየቅ
ለሁሉ እንደሥራው ስትከፍል
የት ይሆን እድል ፈንታዬ
ምን ይሆን መጨረሻዬ 2x
2.
ባገልግሎትህ በቤትህ በልጆችህ ዙሪያ ስገኝ
ምናልባት ትልቅ ዋጋ አለኝ ከሰዎች የተቀበልኩት
ነገር ግን ልብን በምታውቅ ባንተ ዘንድ ያለኝ ምንድነው
የምትሰጠኝ ደሞዜ ከእጅህ የምቀበለው
3.
የመጨረሻው መለከት በምድር ዙሪያ ሲነፋ
በአእላፋት መላክት ታጅበህ ስትመጣ የፅዮን ተስፋ
ነፋሳት ከአራቱ ማዘን ሲሰበሰቡ ልጆችህ
እኔ ግን ዘይቴ አልቆ በምድር የምቀር እንዳልሆን
4.
ሀሌ ሀሌሉያ እያልኩ በጅምላ ዝምብዬ ብሮጥ
በግል በኋላ ኑሮዬ አንተን በሕይወቴ ሳላውቅ
በአንተ መግባት መውጣቴ ለኔ ምን ፋይዳ አለውና
ጌታ ሆይ እንዳስተውል እርዳኝ በግል መመዘን አለና /3/