ባህሩንም ከፍሎ ያሻገራቸውን
በምድረበዳ ውስጥ የመገባቸውን
እኛና ቤታችን እናመልከዋለን
እንደ እያሱ ምርጫ እንመርጠዋለን
1.
እናንተስ ማንን መረጣችሁ ዛሬ
እግ/ርን ወይስ የዓለምን ኩነኔ
በለብታ ሕይወት መኖር አይመችም
በመንታ ልብ ሆኖ መቆም አይቻልም
2.
የፈርኦንን ቤት ታላቅነት ጠልቶ
የእግ/ርን ሕዝብ መሰቃየት አይቶ
ወዶ እንደመረጠ ስቃይ መቀበልን
እንደ ሙሴ ምርጫ እኛም እግ/ርን
3.
በ12 ጥማድ ሲያርስ የነበረው
በብዙ አገልጋዮች በጣም የከበረው
ያንን ሁሉ ትቶ ወዶ እንደመረጠው
እኛም እንደ ኤልሣዕ ምርጫችን ጌታ ነው
4.
በአለም ተንከራቶ እርካታን ስላጣ
የዚህ ዓለም ኑሮ ሰለማያዋጣ
የአባቱን ቤት ተድላ ወዶ እንደመረጠው
እኛም እንደዚያ ልጅ ምርጫችን የሱስ ነው