ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #90 / Song #90

የጽድቅ ዕቃ ጦርን ወገኖች ልበሱ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ወንጌልን በፍጥነት ለዓለም አድርሱ
በርቱ ወገኖቼ ውጊያው ሊያበቃ ነው
}x2ዲያብሎስም አውቋል ጊዜ እንደሌለው
ስለዚህ በቁጣ ወዳኛ ቢመጣም
መሪያችን የሱስ ነው ከቶ እንሸነፍም
1.
የሰላምን ወንጌል በአግራችን ተጫምተን
የመንፈስንም ሰይፍ የእግ/ር ቃል ታጥቀን
የጠላት ሽንገላን እየተቃወምን
ለጨለማው ዓለም ብርሃን እንሁን
2.
በክፉ ፍላፃ በሚንበለበለው
ጠላት እንዳይጐዳኝ ወግቶ በፍላፃው
የእግ/ርን የጽድቅ ጥሩር እለብሳለሁ
ማክሸፊያ ጋሻዬን በእምነት አነሳለሁ
3.
የሥጋን ፍላጐት ላምላክ በማስገዛት
ካንተ እንዲወገዱ ጥርጣሬ ፍርሃት
በጠላት ግዛት ላይ እንድትሆን የበላይ
የመዳን እራስ ቁር አድርግ በራስህ ላይ
4.
ወገባችሁን በእምነት ዝናር ታጠቁና
በኃይሉ ችሎት ፊት ብርቱ እንሁንና
ጸልዩ በመንፈስ በጽናት ትጉና
የደምና ሥጋ ውጊያ አይደለምና
100%
100%