ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #256d / Song #256d

ጠቢብ በጥበቡ አይመካ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 3
1.
አመጻዬ ወደ ምድረ በዳ ወሰደችኝ
ውኃ በሌለው በረሃ አንከራተተችኝ
ለውድቀቴ ዕውቀት ትዕቢቴን አስተማረችኝ
እውነት ስትወቅሰኝ ጥበብ ስትገስጸኝ
ጥማት ሊያቃጥለኝ እልህ ሲታገለኝ
መንፈሱ ሲወቅሰኝ ጌታን አገኘሁኝ
ጠቢብ በጥበቡ አይመካ
ኃያልም በኃይሉ አይመካ
ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ጽድቅንና ፍርድን
በምድር ላይ ማድረጉን ያወቀ
በጌታ ይመካ
2.
ሠማያዊ ጥበብ ዐይንን እከፍታለች
ለሰነፎች ብልሃትን ታስተምራለች
ከምዝምዝ ወርቅና ከቀይ ዕንቁ እበልጣለች
አጥብቀህ ብትይዛት ብትፈላልጋት
ድምጽህን አንስተህ ጥበብን ብትጠራት
ያን ጊዜ ታውቃለህ እግዚአብሔርን መፍራት
3.
የዚህች ዓለም መርማሪ ወዴት አለ
የዘመናት ጥያቄ ያቃለለ
ኢየሱስ ነው ሊቁ ለእኛ የተሰቀለ
ከበረሃው መሃል ሕይወትን ያፈለቀ
የሰይጣንን ስልጣን መትቶ ያደቀቀ
ለእርሱ ስንሸነፍ ጥያቄ አለቀ
100%
100%