ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #32 / Song #32

ስምህ እንደሚፈስ ዘይት ነው /2/

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ደናግል ወደዱት የከበረ ነው /2/
1.
ስምህ የፀና ግንብ ነው የተመሸገ
ክፉውን ዘመን ያልፋል የተሸሸገ
ጽድቅ ወደርሱ ሮጦ ይገባል
በእምነት በስምህ የወጣ ቅጥሩን ይዘላል
2.
በጦሩ ብዛት ታምኖ ሰው ያሸበረ
በቃላት ብዛት ብቻ ልብ የሰበረ
ታላቁ ስምህ በምነት ሲጠራ
ፊትህ ተደፋ አልቻለም ከጦሩ ጋራ
3.
ከናቱ ማህፀን ጀምሮ አንካሣ የሆነ
ሰው የሰለቸው ሁሌ እየለመነ
ሥምህን ሲጠራ እግሩ ይፀናል
እየዘለለ በሰው ፊት ያመሰግናል
4.
መቃብር ወርዳ ታጥቦ የተገነዘ
ዘመድ ወገኑን በሀዘን ያወዛወዘ
ስምህ ሲጠራ ህያው ይሆናል
በፊትህ ቆሞ ድንቅህን ለሰው ያወራል
5.
የእግዚአብሔር ልጅ የሆንከው የማዕዘን አለት
ስምህ ድንቅ ነው ሁልጊዜ ቅባት ያለበት
ከሰማይ በታች ሰው የሚድንበት
የሱስ ስምህ ነው ዘላለም ፅኑ መሠረት
100%
100%