መንፈስህ ከሌለን
የደረቁ ዛፎች ነን
ማደግ የማንችል
1.
በራስ ጥበብና እውቀት መመላለስ
ለአገልግሎት በቤት ውስጥ መተራመስ
ጌታ ያላንተ ከንቱ ነው ህይወትን
ፍፁም አይሰጠው /2/
2.
በዘመርነው በሰበክነው እንድንኖር
ለሰማያዊ መንግሥትህ እንዲያበቃን
በመንፈስህና በእውቀትህ ተገናኘን
ናና በጥበብህ /2/
3.
ክፉን ለማለፍ የሚያስችለን ያ ሀይልህን
በመከራ የሚያጽናና ቅዱስ መንፈስህን
ይላክልን ከፀባኦት በድል ሚመራን
እስከቤትህ /2/
4.
ለእውነት ቃል የሚያቆመን የሚያፀናን
ከእንቅልፋችን የሚያነቃን ሚያበረታን
ዛሬም ይምጣልን ይምራን እስከግብ ዐይናችን
ያብራ አንተን እንድናይ /2/