አመልህ እንደሰው የሱስ አይለዋወጥም
በተግባርህ ፅኑ በቃልህም ታማኝ
ወደአንተ ተጠጋሁ ፍቅርህ ማረከኝ
1.
ምድራዊ ጓደኛ ከቶ አልፈልግም
አንተው ትበቃለህ ሌላም አያሻኝም
ቢኖረኝ ባይኖረኝ ሲቸግረኝ ሳጣም
ካንተ ሌላ ወዳጅ ከቶ አልመኝም
2.
ወደ አባትህ ስትሄድ ቃልህን ነገርከኝ
የሚያፅናና ወዳጅ መንፈስህን ላክህልኝ
አንተ ልማድህ ነው መኖር እንደቃልህ
እንደሰው አይደለህ መቼ ትዋሻለህ
3.
በጣምም ሲጨንቀኝ ምርር ብሎኝ ሳለቅስ
ልጄ አይዞህ ብለህ እንባዬን ስታብስ
ወዳጅ ባጠሁበት ወዳጅ ስለሆንከኝ
ስላንተ አወራለሁ ባይኔ ስላየሁኝ
4.
አንደበቴን ክፈት ሥራህን ላውራ
ምሥጋናን ልዘምር ስምህን ልጣራ
ልቤን ደስ ይለዋል ሀሴትን ይሞላል
ኧራ አይጠገብም ሥራህ መቼ ያልቃል