ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #70d / Song #70d

በምስጋና ላይ ምስጋና

English Translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
በምስጋና ላይ ምስጋና
በምስጋና ላይ ምስጋና
ይገበሃልና።
1.
በከብቶች በረት አድረሃልና
እስከ መስቀል ሞት ታዘሃልና
ለኔ ያደረግኸው ብዙ ነውና
ለስምህ ምስጋና
2.
አምላክ ስትሆን ታስረሃልና
የፈጠርከው እጅ ገርፎሃልና
ይህ ሁሉ ውርደት ለኔ ነውና
ለስምህ ምስጋና
3.
ሁሉ እያለህ ተንከራተሃል
በቁር በሀሩር ወጥተህ ወርደሃል
ይህ ለኔ እንደሆን ጌታ ገብቶኛል
ክብር ይገባሃል
4.
በምድር እንብርት ሶስት ቀን አድረሃል
እስከ ሲኦልም ወርደህ ዘምተሃል
በዚህ ሁሉ ላይ ድልን ነስተሃል
ክብር ይገባሃል
100%
100%