ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #177 / Song #177

ስሙ ኃይል አለው የጌታ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 4
1.
በስሙ ለሚያምኑበት ለሚቀበሉት
የእግዚአብሔርን ልጅነት ስልጣን ለመስጠት
ከሰማይ ሁሉ በታች የሚዳንበት
ከቶ ሌላ ስም የለም ለሰው ደህንነት
የጌታ ስሙ ብቻ ነው
ስሙ ኃይል አለው የጌታ (3x)
2.
አንተ ምስኪን ሽባ ሰው መሄድ ያቃተህ
ብርና ወርቅ የለኝም ላንተ የምሰጥህ
ነገር ግን በኢየሱስ ስም ተነሳ ድነህ
ሲለው ሽባው የዳነው መዝለል የቻለው
ኃይል ባለው በኢየሱስ ስም ነው
3.
መልካም ስጦታ ከላይ የሚገኝበት
ልመና በእግዚአብሔር ፊት የሚቀርብበት
በስሜ ለምኑ የሚል ተስፋ ያለበት
ከቶ ሌላ ስም የለም ከጸሐይ በታች
የኢየሱስ ስሙ ብቻ ነው
4.
ከብዙ ኃያላኖች ብዙ ስም በላይ
ከብዙ ታዋቂዎች ብዙ ስም በላይ
ከስሞች ሁሉ በላይ ታላቅ ስም ያለው
መዳን በስሙ ለሰው ሁሉ የሰጠው
ኢየሱስ ጌታ ብቻ ነው
100%
100%