ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #36 / Song #36

ዘመኑ ሲቀርብ እያየን

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
እንዳንጠፋ ተበትነን
እንዳንርቅ ካንተ ወዲያ
እቅፍ አርገን ባንተ ጉያ
1.
ትንቢቱ ሁሉ ተፈፅሟል
ጌታ መምጫህ ብቻ ቀርቷል
ሁሉም ነገር ሲለዋወጥ
አዘጋጀን እንዳንናወጥ
2.
የትንቢቱ ጣፋጭ ፍሬ
መራር ሲሆን ፈጥኖ ዛሬ
ፍቅር በርዶ ሰው ሲራራቅ
እርዳን ሥፍራችንን እንዳንለቅ
3.
ወዳጅ ሁሉ ሲከዳዳ
እህት ወንድም ሲሆን ባዳ
ወዶ አይደለም ይህ የሚሆነው
የትንቢቱ ፍፃሜ ነው
4.
አለም ክፋቷ ሲበዛ
እንዳናያት አንደዋዛ
እንዲህ ሁሉ ሚራወጠው
የጌታ ምፃት ደርሶ ነው
100%
100%