ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #310d / Song #310d

ስላወጣሀኝ ተራራ

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 4
ስላወጣሀኝ ተራራ
ስላሳለፍከኝ መከራ
ስላሻገርከኝ ማዕበል
ተመስገን እንጂ ምን ልበል
1.
ለማለፍ ሩቅ የሆነ
ተስፋዬን ያመነመነ
የወጋኝ በነጋ ጠባ
አላውቅም የት እንደገባ
2.
የዛሬ ተስፋ ጨልሞ
ለሊቱን እጅግ አርዝሞ
በጎኔ እሾህ የሆነ
ሲነጋ ወዴት በነነ
3.
መንገዴን በእሾህ የዘጋ
ወጥመዱን ለእግሬ ዘረጋ
አለፍኩኝ ከእጁ አምልጬ
የእባቡን ራስ ረግጬ
4.
አልሞትም በህይወት እኖራለሁ
የጌታዬን ስራ አወራለሁ
የሞቴን መርዶ የሰማችሁ
አለሁኝ ደስ ይበላችሁ
5.
አልሞትም በህይወት እኖራለሁ
የጌታዬን ስራ አወራለሁ
የሞቴን መርዶ የሰማችሁ
አለሁኝ ደስ ይበላችሁ
100%
100%