ኢየሩሳሌም ናት የኔ ናፍቆት 2X
ኢየሩሳሌም ናት የኔ ምኞት 2X
1.
ነጭ ልብሴን ለብሼ የምኖርባት
ተስፋዬ ተሟልቶ በክብር የማርፍባት
ከበጉ ጋር እኔም በድል አድራጊነት
ሁሉንም አልፌ ምንፈላሰስባት
2.
ከነገድና ከቋንቋ የተዋጁ
ዲያብሎስን ጥለው ድል የተቀዳጁ
አደባባይዋን ለመርገጥ ሙሉ ስልጣን
ያላቸው ቅዱሳን ናቸው ብፁዓን
3.
እንደብርሌ የሚያንፀባርቅ ወንዝ ያለበት
የሚያረካ የሕይወት ውሃ የሚፈልቅባት
እፁብና ድንቅ ይሆነችው ከተማ
ኢየሩሳሌም የለባትም ጨለማ
4.
በታረደው በግ በጌታ ኢየሱስ ደም
በታነፀችው በዚያች ቅድስት ሀገር
መነካከስ መጐሻሸም ጭራሽ የለም
ሰላምም አይደፈርስም ለዘላለም