ከሚቆየን ክብር ጋራ
ሰቆቃው ቢበዛም በምድር
ከቶ አይችልም ሊወዳደር
1.
ከሚመጣው የክብር አክሊል ጋራ ሲመዛዘን
ሲለካና ሲታይ በምድር ሚደርስብን ሀዘን
እጅጉን ይበልጣል ጌታችን ለኛ ያዘጋጀው
እንደ ጉድፍ ጥራጊ አድርገን ሁሉን እንቁጠረው
2.
ጭንቀትና ሁከት ጥላቻ መገዳደል ዛቻ
ወንድም ወንድሙን ሊያጠምደው ሁልጊዜ ዘመቻ
የሚታየው ነገር በሙሉ ልብ የሚያደማ ነው
ብርሃን የሌለበት ውጥንቅጥ ድቅድቅ ጨለማ ነው
3.
እውነትና ፍቅር ተረግጦ ጥላቻ በርትቷል
አለምም በዚሁ ሥራ ላይ እጅግ ተሰማርቷል
እኛ ግን ከአለም ተግባር ጋር ከቶ አንተባበር
እድል እንዲኖረን ሁላችን በላይኛው ሀገር
4.
የሚሞተው በማይሞት ክብር እስኪተካ ድረስ
በሚሞተው ሥጋችን ዛሬ ያለም ሥራ አይንገስ
በዚህ ውስጥ አልፈንም ለመቆም እንቀጥል ትግላችን
የሚመጣውን ክብር ለመልበስ እንቁም በእምነታችን