ሌሎችንም ከማዳን ልባችን እጅግ ዝሏል
ስለዚህ እንነሣ ከልባችን እንሩጥ
የወንጌሉንም ሚስጥር ለሰዎች እንናገር
1.
ነፍሳት ሳይማረኩ የወጡት ሳይመለሱ
ሊመጣ ነው ንጉሡ /2
2.
እኛማ ፀጋው ደልቶን ክፉ ያለም አይመስለንም
ስለዚህ አመስግነን መጋደምን ለመድን
ግን እንደዚህ አይደለም ምድር በሁከት ላይ ናት
የዘመናችን ጌታ ማዳኑን እንግለጽለት
3.
ቀድሞ የአምላክን እጅ በበጐ የለመዱ
ዛሬ እርካታን አጥተው በተራራ የሄዱ
ለመሮጥም ያልቻሉ ድካም እጅግ የያዛቸው
ብዙ ወገኖች አሉ እንሂድ እናበርታቸው
4.
ሰምተውመ የታከቱ አለምን የወደዱ
ድካም አይሎባቸው ወደኋላ የሄዱ
አሉና እኛም እንሩጥ ጉልበታችን ይበርታ
እርሱንም እናስበው ቀኑ ደርሷል የጌታ