ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #162 / Song #162

ንጉሱ በቤቱ ግብዣ አዘጋጅቷል

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ንጉሱ በቤቱ ግብዣ አዘጋጅቷል
ድግሱን ለመብላት ሁሉንም አድሟል
ፈቃደኛ ማነው በፍጥነት የሚራመድ
የራሱን ሥራ ትቶ ወደዚያ የሚሄድ
1.
ንጉሱ ሲጠራ ሲደርሰን መልዕክቱ
የሠርጉን ልብስ ለብሰን እንገኝ በፊቱ
2.
በሠርጉ አደራሽ በዚያ ለመገኘት
ቅድሚያ ያስፈልጋል የሕይወት ዝግጅት
ልብሳችንን አጥበን በደሙ ከነፃን
መግባት እንችላለን እንድንድንበት
3.
በሠርጉ እንዲገኙ ብዙዎች ቢጠሩም
መገኘት አልቻሉም ይዟቸው ይህ አለም
ስለዚህ ሂዱና ጥሩልኝ ሌሎችን
ከዚህ ዓለም ጋራ ያልተቆራኙትን
4.
ሠርጉን ያዘጋጀው ንጉሱ የሱስ ነው
በዚያ መገኘቱ ለእኛ ክብር ነው
ነገር ግን ነጩን ልብስ ለብሰን ካልተገኘን
ከሠርጉ አዳራሽ እንወገዳለን
100%
100%