አንተ ነህ ተስፋዬ የሕይወቴ አለኝታ
እጆቼ ተዳክመው ብለቅህም እንኳ
አይዞህ/ሽ/ በርታ/ቺ/ ልጄ አልለቅህም/ሽም/ በለኝ አልተውህም/ሽም/ በለኝ
1.
እባክህ አምላኬ ከፊትህ አትጣለኝ
እባክህ ጌታዬ ከአንተ አታርቀኝ
ካንተ ስርቅ እኔ በጣም ደካማ ነኝ
እባክህ አምላኬ አልለቅህም በለኝ አልተውህም በለኝ
2.
በወገኔ መኸል የሆንኩ ሱነማዊት
እግ/ር የሰጠኝ ሕፃን ልጄ ቢሞት
ፈጽሞ አልተውህም አለቅህም ብለው
የሞተውን ልጄን በሕይወት አኖረው /2/
3.
አታላይ ያዕቆብ መባሉ ሰልችቶኝ
የስደት ባርነት ኑሮው አንገፍግፎኝ
አልለቅህም ብለው ጌታ ካልባረከኝ
ስሜን ቀይሮልኝ በበረከት ሞልቶኝ ለሀገሬ አበቃኝ
4.
ፈተና ቢበዛም ዛሬ በሕይወቴ
ከቶ ስላልተወኝ የሰማይ አባቴ
በምንም አልሰጋም ስላለ ረዳቴ
ይመራኛል የሱስ እስከ ሰማይ ቤቴ /2/