አንተ እረኛ በጐቹን ጠብቅ
እንዳይበተኑ ለአራዊት መብል
በምን ቸገረኝ ቸል ብለህ ሳለህ
ከተበተኑ /ከተነጠቁ ትጠየቃለህ
1.
ወይ አንተ አልገባህ የሚገቡትን ትከለክላለህ
ፃዲቃንን ሁሉ በክፉ ሥራ ትመልሳለህ
ከላይ እግዚአብሔር ይጠይቅሃል
አቤል ወንድምህ ወዴት ነው ይልሃል
2.
የደከመውን የቦዘነውን አላጸናህም
የታመመውን የተሠበረውን አልጠገንከውም
ስለዚህ እግዚአብሔር ከላይ ይጮኸል
ክፉ እረኛ ወዮልህ ይልሃል
3.
በምድር ያሉትን ጣኦታትን ሁሉ ትፀየፋለህ
መቅደሱን በመዝረፍ ከፍ ያለውን ጌታ ታሳፍራለህ
በአንተ ሠበብ የአምላክህን ስም
በሠማይ ያለውን ታሰድባለህ
4.
ልወድቅ ያለውን ዘንበል ያለውን ቤት አይተህ አልፈሃል
በምላስህ ጦር ወንድምህን ወግተህ አስመርረሃል
እግዚአብሔር አምላክ ይገስጽሃል
ከክፉ ሥራህ ተመለስ ይልሃል