ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #14 / Song #14

ሰሚ ጆሮ አስተዋይ ልቦና

english transilation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 2
ሰሚ ጆሮ አስተዋይ ልቦና
ጌታ ሆይ ስጠን /4/
እውነትን በሀሰት መለወጣቸው
ፈጣሪን በፍጡር መተካታቸው
ልባቸው ከእግ/ር ደንድኖ መራቃቸው
እንዴት ያሳዝናል አለመዳናቸው
1.
የኖህ ዘመን ታሪክ ጠንቅቀን ስናየው
ለጥፋት የበቁት እውነት በመናቅ ነው
ወደ መርከብ ግቡ ዘወትር ሲባሉ
የሚሰማ ጠፍቶ በውሃ ተበሉ
2.
የኔም መጨረሻ ጥፋት እንዳይሆን
ካሁኑ እንድዘጋጅ ቀድሰው ልቤን
እኔም ቶሎ ቶሎ ዘመኑን ልመርምር
መስተዋልን ስጠኝ እንደቃልህ ልኑር
3.
ዛሬም በዚህ ዘመን ያለህ ቤተ-እስራኤል
እውነት ሊንገርህ ጠንቅቀህ አስተውል
በፀሎት በምልጃ ቅረብ ወደ አምላክህ
ተጠቀም በጊዜህ ምህረት ሳያልፍብህ
100%
100%