ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #45 / Song #45

ስኮንዶች ደቂቆች ከንፈዋል

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: unknown
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 1
ሰዓታት ቀናትም አልፈዋል
ቀንና ማታን አፈራርቆ
ሣምንታት ወራትን ጠብቆ
በጋ ክረምት ጊዜውን አውቆ
ፀሐይ በዝናብ ተፈራርቆ
1.
ከወቅቶች ወቅቶች አሸጋግሮ
አሮጌውን በአዲስ ቀን ቀይሮ
ለአዲስ ዘመን ጌታ አደረሰን ተመስገን /3/
ለአዲሱ ዓመት በቃን
2.
ዘመናትን በቸርነትህ ታቀናጃለህ
ዓመታትን ወራትንም ታስኬዳለህ
ሣምንታትን ቀናትንም ተቆጣጥረህ
አሳለፍከን የኛ አምላክ ሁሉን ቻይ ነህ /3/
3.
በአውሎ ንፋስ ጐርፍ መከራ
አለም በሽብር ተወጥራ
ረሃብ ጦርነት በጋራ
ሲፈራረቁበት በተራ
አምላክ ስላለ ከኛ ጋራ
የአለምን መከራ ሳንፈራ
4.
ከቀን ቀን በቸርነቱ አልፈን
ከክፉ አደጋ ከልሎን
ተመስገን /3/
ለአዲሱ ዓመት በቃን
5.
ከቻምናስ ዓመቱ መጥፎ ነው
አምናም ቢሆን እንደካቻምና ነው
ዘንድሮስ ኖረናል አይባልም
ዓለም እንዲህ እያለ ቢያማርም
እኛስ የሱስ ጌታን ይዘናል
ሁሌ በጌታ ደስ ይለናል
6.
ከቁጥርም ቁጥር አብዝቶ
ጌታ በመንፈሱ አጠንክሮን
በቤቱ ለክብሩ ቆመናል
ተመስገን /3/
ለዚህ ያደረስከን
100%
100%