ወደ መነሻ / Back to Home
መዝሙር #48d / Song #48d

ይህን ደም ግባት ያገኘሁት

english translation

ምድብ / Category: ምስጋና / Praise
ደራሲ / Author: ወላይታ ቃለ ሕይወት ሀ-መዛምራን
ዓመት / Year: 2025
👁️ Views: 4
1.
እውር ነበርኩኝ አየሁኝና
የጨለመብኝ ተገፈፈና
እኔም ወግ ደረሰኝና
አማረብኝ ብርሃን አየሁና።
ይህን ደም ግባት ያገኘሁት
ወዝ አግኝቼ ያማረብኝ
ካንተ የተነሣ እኔ ተዋብኩኝ
ክበርልኝ ያከበርከኝ።
2.
ደንቆሮ ነበርኩ መስማት የማልችል
የሚሉኝ ምንም የማይገባኝ
ደርሰህ ስትረዳኝ አባባ
ተከፈተልኝ ጆሮዬም ሰማ።
3.
ብለብስም ፍጹም የማያምርብኝ
ብጠጣም ደግሞ ውበት ማይኖረኝ
የሱስ አንተ ስትቀርበኝ
አማረብኝ ውበትን ጨመርኩኝ።
4.
አንተ ወደክኝ ተወደድኩኝ
አክብረኸኝም ተከበርኩኝ
አንተ ስትሆን አብረኸኝ
አማረብኝ ውበትን ጨመርኩኝ።
100%
100%